በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄይቲ በወታደራዊ ኃይል ጥበቃ ስር ውላለች


የሄይቲ ፕሬዚደንት ዦቬኔል ሞይሲ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሌሊት በአጥቂዎች ጥይት ተገድለዋል
የሄይቲ ፕሬዚደንት ዦቬኔል ሞይሲ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሌሊት በአጥቂዎች ጥይት ተገድለዋል

የሄይቲ ፕሬዚደንት ዦቬኔል ሞይሲ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሌሊት በአጥቂዎች ጥይት መገደላቸው ተከትሎ ሃገሪቱ በወታደራዊ ኃይል ጥበቃ ስር መዋሏን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ።

የሽግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ ክሎድ ጆሴቭ ትላንት ረቡዕ ጠዋት በመንግሥቱ ቴሌቭዢን ቀርበው በሰጡት መግለጫ የአስተዳደሩን አመራር መያዛቸውን ገልፀው ወታደራዊ ዐዋጅ ደንግገናል ብለዋል።

ፕሬዚደንት ዦቬኔል ሞይሲ በዋና ከተማዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ ጠርዝ ላይ በሚገኘው ፔሌሪን በሚባለው የባለጸጎች ሰፈር የግል መኖሪያ ቤታቸው ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው መገደላቸውን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልፀዋል። የሀገሪቱ ድንበር ኬላዎች እና ዋናው የአውሮፕላንማረፊያ መዘጋቱንም ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሄይቲ ፕሬዚደንት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘው ለሃገሪቱ ሕዝብ ሐዘናቸውን መግለጻቸውን ከዋይት ሃውስ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

"በጥቃቱ የቆሰሉት የሄይቲው ፕሬዚደንት ባለቤትም ፈጥነው እንዲያገግሙ ልባዊ ምኞቴን አስተላልፋለሁ" ያሉት ፕሬዚደንት ባይደን ሄይቲን ለመርዳት ዝግጁ ነን፤ ጸጥታዋ እንዲጠበቅ መሥራታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።

የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር በመግለጫቸው እንዳሉት ትናንት ከሌሊቱ ሰባት ሰዐት ላይ የተፈጸመው የግድያ ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ በሰለጠነ እና በታጠቀ ቡድን እንግሊዝኛ እና የስፓኝ ቋንቋ የሚናገሩ አባላት በደምብ ተቀናጅቶ የተካሄደ ነው።

የፕሬዚደንቱ ባለቤት ቆስለው ለህክምና ሆስፒታል መወሰዳቸውን እና በጥቃቱ ወቅት ቤቱ ውስጥ የነበረው ወንድ ልጃቸው ደግሞ ጥበቃ ወደሚያገኝበት ቦታ መወሰዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG