ሃዋሳ —
የኢትዮጵያ ዐሥረኛው ክልል ሆኖ ከተደራጀ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ሲዳማ ክልል ፖለቲካዊ ትያቄው ቢመለስም ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ችግሮቹ መፍትኄ እንዳልተሰጠው አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የሲዳማ ሕዝብ ለክልል አደረጃጀት የታገለው በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ውስጥ ንቁ እና ብቁ ተሳታፊ ለመሆንና በራሱ የራሱን ልማት ለማፋጠን በማለም መሆኑን የገለጹት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፤ የፖለቲካውን ጥያቄ ብናረጋግጥም የሕዝቡን የዕድገት ፍላጎት ገና አልመለስንም ብለዋል።
የሲዳማ ሕዝብ በክልል የተጀራጀበትን አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል እያከበረ ይገኛል።
(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)