የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል የወጣው በአራት ግንባሮች ተከፍሎ ከአንድ ወርበላይ በቆየ ሂደት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ። በትግራይ ክልል ያለውግጭት ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ያለበት መሆኑንና በብዙዎች ዘንድ ግጭቱ እንዲቆም እንደማይፈለግ ትላንት ሰኞ ሰኔ 28/2013 ዓ.ም ለሕዝብ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላትየተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዚህም ዓላማ “ትግራይን ጨምሮ ኢትዮጵያን ማዳከም ነው” ብለዋል፡፡
የሕወሓት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ በሰጧቸው መግለጫዎች፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት መቀለን ጨምሮ ከክልሉ የወጣው፣ ተሸንፎ መሆኑን ቢገልጹም፣ ጠቅላይ ሚኒስትርዐቢይ ግን፣ መንግስታቸው ጥናት በማድረግ፣ ባሳለፈው ውሳኔ ማስወጣቱን ገልጸዋል፡፡ሪፈረንደም (ሕዝበ ውሳኔ) ብለው በገለጹት ምርጫ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ጠንካራ መንግሥት እንደሚፈልግ አሳውቋል ያሉም ሲሆን፣ “ይህን ለመቀልበስ የሚነሳ ማንኛውም ሐሳብ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።
እስካሁን የነበረውን ዓይነት መንግሥታዊ መዋቅር እንዲቀጥል የመንግሥታቸውፍላጎት እንዳልሆነ ገልጸው፤ በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችእንደየተሳትፏቸው በመንግሥት የአስፈጻሚ መዋቅር ውስጥ እንደሚካተቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በትላንቱ አራተኛ ልዩ ስብሰባው፣ ለ2014 ዓ.ም የቀረበውን፣ 561 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር በጀትም አጽድቋል፡፡
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)