በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ተዋጊ ኃይሎች አዛዥ ለትግራይ ክልል ግጭት ፖለቲካዊ መፍትኄእንዲሰጥ ጠየቁ


“የኢትዮጵያ መንግሥት በጦርነቱ ሊያሸንፍ ስላልቻለ በድርድር ተኩስ አቁምእናድርግና ለክልሉ ግጭትም ፖለቲካዊ መፍትኄ ይሰጥ” ሲሉ የትግራይ ታጣቂኃይሎች አዛዥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ሳምንት በፊት ወታደሮቹን ከትግራይ ክልል ዋናከተማ ከመቀሌ ማስወጣቱን ተከትሎ ሮይተርስ የትግራይ ተዋጊ ኃይሎች አዛዡጄነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ ካልታወቀ ሥፍራ በሳተላይት ስልክ ሰጡኝ ባለው ቃል"የአብይ ኃይሎች ስለተሸነፉ ተኩስ አቁም ለማድረግ እንደራደር እያልን ነው" ማለታቸውን ከናይሮቢ ባጠናቀረው ዘገባ ጠቅሷል።

አስከትለውም “ላለው አጠቃላይ ችግር ዕውነታ ላይ የተመሠረተ መፍትኄ እንዲገኝብለን ራሳችንን እየገታን ነን፤ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን እንዲረዳልንእጠይቃለሁ” ማለታቸውን ዘገባው ጠቁሞ “ሌላ አማራጭ ከሌለ ግን በወታደራዊመንገድ ለመፍታት መሞከር ይኖርብናል" ማለታቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያመንግሥትን መልስ እንዳላገኘ የዜና ወኪሉ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት “ስትራተጂያዊና ሰብዓዊ ምክንያት” ባለው እርምጃወታደሮቹን ከትግራይ ማስወጣቱ ሲታወቅ ሕወሃት ግን “ተኩስ አቁም አደረግንየሚሉት ፌዝ ነው፤ የወጡት ተባረርው ነው” ማለቱን ዘገባው አውስቷል።

ዕሁድ ዕለት ሕወሃት ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር ማናቸውንምየተኩስ አቁም ለማድረግ በቅድሚያ የኤርትራ እና የአጎራባች አማራ ክልል ወታደሮችበሙሉ መውጣትና ሌሎችም ነጥቦችን የዘረዘረ ቅድመ ሁኒታ አስምቀምጡዋል

የትግራይ ተዋጊ ኃይሎች አዛዡ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይበጦርነቱ መሸነፋቸውን የማያምኑ ከሆኑ ውጊያው ይቀጥላል፤ የኢትዮጵያመንግሥት ሆን ብሎ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ እያደረገ ነው፤ ወታደሮቹ ከወጡወዲህ እርዳታ መግባት አልቻለም” ማለታቸውን አክሏል።

ሮይተርስ አክሎም “ባሁኑ ወቅት ሕወሃት የማረካቸው 8000 ወታደሮች አሉ” ማለታቸውን የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ግን“የምርኮኞቹ ቁጥር የተጋነነ ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ ትክክለኛውን ቁጥርለማረጋገጥ እንዳልቻለ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ባደረጉትንግግር “ሰላማዊ መፍትኄ ስለፈለግን ነው እንጂ ካስፈለገ አንድ ሚሊዮን ወጣቶችበፈቃደኝነት ለውጊያ ይመዘገባሉ፤ ጦርነቱን መቀጠል ይቻላል፤ ውጤቱ ግንበሁለቱም በኩል ሕይወት መጥፋት እና ዶላር ማባከን ነው፤ በዚህ መንገድ ማሸነፍአንችልም” ማለታቸውን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG