ኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በውሃ መሙላት መጀመሯን በይፋ የተናገረችው ግብፅ፤ሙሌቱ የአንድ ወገን እርምጃና የቀጠናውን ደህንነት እና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥልነው በማለት ተቃውሞ ማሰማቷን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
በትናንትናው ዕለት ግብጽ ኢትዮጵያ ለናይል ወንዝ ዋነኛ ገባር በሆነው አባይ ወንዝላይ የገንባችውን የኅዳሴ ግድብ በውሃ መሙላት መጀመሯን አስታውቃለች።የጸጥታው ምክር ቤት አለመግባባቱን በሚመለከት ስብሰባ ለማድረግ ቀንበቆረጠበት ሰሞን የተሰማው የኢትዮጵያ እርምጃ ውጥረቱን እንዳያባብሰውተሰግቷል።
ግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል የወጣው መግለጫ ፣ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደልአቲ ከኢትዮጵያው አቻቸው፤ ኢትዮጵያ የሁለተኛውን ዓመት የውሃ ሙሌትመጀመሯን የሚያስታውቅ ኦፊሳሊያዊ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ይገልጻል ።
መግለጫው ይሄንን “ የአንድ ወገን እርምጃ” ፣ በ2015 የአውሮፓውያን የቀንአቆጣጠር የተገባውን ስምምነት “በግልጽ እና በከፋ መልኩ የጣሰ ነው” በሚልአሻሚነት በሌለው ሁኔታ ውድቅ እንዳደረገችው አስታውቋል። አያይዞም እርምጃለቀጠናው ደህነነት እና ሰላም ስጋትም ነው ብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዐስርት ዓመታት ያስቆጠረውን ውዝግብበተመለከተ ውይይት ለማድረግ ለሐሙስ ሐምሌ 1/2013 ዓ.ም ስብሰባ ጠርቷል።በሚያዚያ ወር የአፍሪካ ኅብረት በአደራዳሪነት የተሳተፈበት ንግግር ሳይሰምርመቅረቱን ተከትሎ፣ ባለፉት ወራት ውስጥ ውጥረቱ እያየለ መጥቷል።
የግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጸጥታው ምክር ቤትን ስብሰባለመታደም በኒዮርክ ከተማ ይገኛሉ። የግብጹ ፕሬዚደንት አብደል ፈታ ኤል ሲሲየግብጽን የውሃ ድርሻ የሚቀንስ ማናቸውም የኢትዮጵያን እርምጃ መንግሥታቸውእንደማይታገስ አስጠንቀቀዋል። የግብጽ የውሃ ድርሻ ከተነካ ሀገራቸውማናቸውንም ዓይነት እርምጃዎች ልትወስድ እንደምትችል ያስጠነቀቁት ሲሲ፣ አዲስአበባ ከካይሮ እና ካርቱም ጋር በመተባባር ማንኛውንም ግጭት እንድታስቀር ቀደምባለው ጊዜ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ዜና ምንጭ ይፋ እንዳደረገው የግድቡ 80 በመቶ ግንባታየተጠናቀቀ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ኃይል የማመንጨት ሙሉ አቅሙ ላይይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ግድቡ ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ፣ ከዓለምደግሞ ሰባተኛው ግዙፍ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንደሚሆንም ተነግሯል።
የአሁኑ ያለመግባባት ያነጣጠረው ፤ ኢትዮጵያ ግድቡን በምን ያህል ፍጥነትመሙላት እና ዳግም ሙሌት ማከናወን እንዳለባት፣ ዓመት ተሻጋሪ ድርቅ በሚኖርበትጊዜ ለታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ምን ያህል ውሃ መልቀቅ እንዳለባት በሚሉና ሌሎችተያያዥ ጉዳዮች ላይ ነው።
ግብጽ እና ሱዳን ዮናይትድ ስቴትስ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአውሮፓኅብረት ግድቡ ተግባሩን የሚከውንበት ሂደት እና አሞላሉን በተመለከተ በሕግገዥነት ያለው ስምምነት ላይ እንዲደረስ እገዛ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ጥሪአቅርበዋል።
ከ90 በመቶ በላይ ለሆነው የውሃ ፍጆታዋ የአባዕን ወንዝ የምትጠቀመው ግብጽ ፣ሁኔታዎች ሳይገናዘቡ ግድቡ ሥራ ቢጀምር የሚያስከትለው አደገኛ ውጤትያሰጋታል። አብዛኛው ሕዝቧ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ተጠቃሚ ያለመሆኑንየምታነሳው ኢትዮጵያ በበኩሏ በ5 ቢሊየን ዶላር ወጪ በመገንባት ላይ ያለችውግድብ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቃለች።
ሱዳን ኢትዮጵያ የግድቡን እንቅስቃሴ በተመለከተ መረጃ እንድታስተባባር እናእንድታጋራ ትፍልጋለች። ይሄ እንዲሁም የምትሻው ደግሞ በጎርፍ መጥለቅለቅንለመከላከል፣ በናይል ወንዝ አውራ ገባር ወንዝ ጥቁር አባይ ላይ የሠራቻቸው የራሷኃይል አመንጪ ግድቦችን ከጥፋት ለማዳን ነው። ነጭ አባይ እና ጥቁር አባይ ካርቱምላይ ይገናኛሉ። አንድ ወንዝ ሆነው ወደ ሰሜኑ አቅጣጫና ወደ ግብጽ ከዚያም ወደሜዲትራኒያን ባህርም ያቀናሉ።
(የአሶሼትድ ፕረስን ዘገባ ወደ አማርኛ የመለሰው ሃብትሙ ስዩም ነው)