በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያን ያካለሉት ወጣት ሰላም ተጓዦች ማስታወሻ


.
.

በተለያዩ ስፍራዎች ግጭቶችን ባስተናገደችው ኢትዮጵያ የሰላም ዕጦት የብዙሃን አንገብጋቢ ችግር ነው። ይሄን የተረዱ ወጣቶች ለሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ይበጃሉ የሚባሉ በጎ ተግባራትን እና አስተማሪ መርሀ ግብሮችን እያከናወኑ ይገኛሉ።ዛሬ ለውይይት የጋበዝናቸው ሁለት ወጣቶች በመሰል እንቅስቃሴዎች ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።

ዮናስ ቦስኮ እና ሶሊያና እሸቱ ይባላሉ። ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የተለያዩ ስፍራዎችን የሚያካልል “የሰላም ጉዞ” በእግር እና በመኪና አድርገዋል። በደረሱበት ስፍራ ፣ ካገኟቸው የተለያዩ ህዝቦች ጋር የባህል ልውውጥ አድርገዋል፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ተምረዋል።

ከወጣቶቹ ጋር አጭር ውይይት ያደረገው ሀብታሙ ስዩም፣ ስለ ጉዟቸው አጠቃላይ ሂደት እና ተያያዥ ጉዳዮች ለማወቅ ጥሯል። ሙሉ ቆይታቸውን እንድታዳምጡ እንጋብዛለን ።

ኢትዮጵያን ያካለሉት የሰላም ተጓዦች ማስታወሻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:18 0:00


XS
SM
MD
LG