No media source currently available
ኢትዮጵያና ጂቡቲ በድንበር ተሻጋሪ ውሃ ልማትና ኢንቨስትመንት ላይ መከሩ። የኢትዮጵያና ጂቡቲ ከፍተኛ አመራሮች በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን የሚገኘውን የኢትዮ - ጂቡቲ ድንበር ተሻጋሪ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። በፕሮጀክቱ አሉ የተባሉ ክፍተቶች የተገመገሙ ሲሆን የጂቡቲ ባለሃብቶች በሶማሌ ክልል መዋዕለ ነዋያቸውን በሚያፈሱበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል።