በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትራምፕ ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ለአፍሪካ ምን ሊመስል ይችላል?


ፋይል - በትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን ባለቤታቸው ሜላንያ ትራምፕ ጋና፣ ማላዊ፣ ኬንያ እና ግብፅን ጎብኝተው ነበር።
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:58 0:00

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሥልጣን እየተመለሱ ባሉበት ወቅት ከአፍሪካ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተለይ ከፀጥታ እና ደህንነት ትብብር አንፃር ምን ሊመስል ይችላል የሚለው ጥያቄ ጎልቶ ይነሳል። አፍሪካ ለአሜሪካ ቀዳሚ የፖለቲካ፣ የደህንነት እና የስትራቴጂ አቅጣጫ አለመሆኗን የሚገልጹት የአፍሪካ ጉዳይ ተንታኞች፣ ትራምፕ በአፍሪካ ላይ ያላቸው ትኩረት እንደ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ ሀያል ሀገራትን በመገዳደር ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG