በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ ኮሚቴ በትግራይ ጉዳይ እማኝነት አዳመጠ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀ መንበር ዲሞክራቱ ግሬገሪ ሚክስ “ትግራይ ውስጥ የደረሰው በሰብዕና ላይ የተፈፀመ ወንጀል፤ የዘር ማጥፋትም ሊሆን ይችላል” ሲሉ ተናገሩ። እንደራሴው አስተያየታቸውን የሰጡት በኢትዮጵያ ግጭቶች ጉዳይ ላይ እማኝነት ለማድመጥ ዛሬ ለተቀመጠው የኮሚቴው ስብሰባ ነው።

የኮሚቴው አንጋፋ ሪፐብሊካን አባል ማይክል መኮል በበኩላቸው "በኔ አመለካከት በትግራይ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል፥ በሰብዐዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸም ወንጀል እንዲሁም የዘር ማጥፋት አድራጎት ተፈፅሟል” ብለዋል።

በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ፊት የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ “በጉዳዩ ላይ የፍትኅን እና የህግን ጉዳይ መሠረት ያደረገ ግምገማ በሰፊው ተካሂዷል” ብለዋል። “በግምገማው የተዘረዘሩት ማስረጃዎች በሰብዕና ላይ የተፈፀመ ወንጀል፥ ወይም የዘር ማጥፋት አድራጎቶች ይሁኑ አይሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ውሳኔ መስጠት ይኖርባቸዋል” ሲሉ ለኮሚቴው አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

XS
SM
MD
LG