ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ኃይሎች ከትግራይ ክልል መዲና መቀሌ መውጣታቸው፣ ውጊያው ሙሉ በሙሉ አብቅቷል ማለት እንዳልሆነ አንዳንድ ቀጠናዊ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። በዮናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም ውስጥ የሚሰሩት እና በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉት አሊ ቨርጅ በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ ድምጿ ኬት ፓውንድ ዳውሰን ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሊ ቨርጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሦስት ወራት በላይ ተቆጣጥሯት የነበረችውን የትግራይ ክልል መዲና በዚህ ሰዓት ለቅቆ ለመውጣቱ የሚሰጡ መላምቶችነም ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፣
“ሁለት ተጻራሪ ትንታኔዎች አሉ። አንደኛው የትግራይ ኃይሎች እርምጃ ኃያልነት የፌዴራሉ መንግሥትን የተኩስ አቁም እንዲያውጅ ገፋፍቶታል የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ ይህ እየተባባሰ የመጣውን የሰብዓዊ ጥፋት የተረዳው እና አንዳች እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ያመነው የፌዴራል መንግሥቱ ዕቅድ ነው የሚል ነው። እንደሚመስለኝ እውነታው የሁለቱም ቅልቅል ነው። መዘንጋት የሌለበት ነገር ከሳምንት በፊት የፌዴራሉ መንግሥት የአየር ድብደባ ሲፈጽም እንደነበረ ነው። ከትግራይ ኃይሎች የታየው መገዳደር ውሳኔው የተላለፈበትን ቀን ያፋጠነው ይመስላል።”
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።