በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮና በትምህርት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደቀጠለ ነው 


የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የፅዳት አገልግሎት ሲሰጡ
የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የፅዳት አገልግሎት ሲሰጡ

ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለዘጠኝ ወራት ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶች አሁን በፈረቃ ማስተማር ቢጀምሩም ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩት ተማሪዎች ላይ ያሳደረው ጫና ግን እንደቀጠለ መሆኑን ተማሪዎች ይገልፃሉ። በወረርሽኙ ምክንያት የመተዳደሪያ ገቢያቸውን ያጡ ወላጆችም የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪ ለመሸፈን በመቸገራቸው አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሳይመለሱ ቀርተዋል።

ኮሮና በትምህርት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደቀጠለ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:23 0:00


በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተዘግተው በቆዩባቸው ዘጠኝ ወራት ተማሪዎች ለ-ያለእድሜ ጋብቻ፣ አስገድዶ መደፈር፣ የጉልበት ብዝበዛና ሌሎች ተያያዥ የስነ ልቦና ችግሮች ተጋልጠዋል። በቤት ውስጥ ሆነው እንዲማሩ ለማድረግ የተደረጉት ጥረቶችም ብዙም ስኬታማ አልነበሩም።

እነዚህን ችግሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርት ሚኒስቴር በወሰደው ርምጃ፣ ካሳለፍነው ጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል። የመማር ማስተማሩ ሂደት የተማሪዎችንና መመህራንን ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሆንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ፣ ርቀታቸው ጠብቀው እንዲቀመጡና በፈረቃ እንዲማሩ አማራጮች ቀርበዋል።

ሆኖም ኮቪድ 19 በተማሪዎችና በወላጆቻቸው ላይ ያሳደረው ጫና ግን አሁንም እንደቀጠለ ብዙዎች ይናገራሉ። በተለይ ወረርሽኙ በኢኮኖሚ ላይ ባሳደረው ጫና ወላጆች የገቢ ምንጮቻቸውን በማጣታቸውna andand ልጆች የወላጆቻቸውን ገቢ ለመደጎም ወደ ስራ በመሰማራታቸው ሙሉ ለሙሉ ወድ ትምህርታቸው መመለስ አልቻሉም።

ወይዘሮ አልማዝ ወርቁ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ አንድ ነዋሪ ሲሆኑ ሁልት ልጆቻቸውን ለማስተማር በከተማው የአውቶቢስ መናኸሪያ የተለያዩ ስራዎችን ይሰሩ ነበር። ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመጣ በኃላ ግን በመናኸሪያው ስራ መስራት ባለመቻላቸው ገቢያቸው ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ይናገራሉ።

በገቢያቸው መቋረጥ ምክንያት ወይዘሮ አልማዝ እንደቀድሞው ልጆቻቸውን በአግባቡ ወደ ትምህርት ቤት መላክ አልቻሉም። በተለይ የመጀመሪያው ወንድ ልጃቸው የሚማርበት ትምህርት ቤት እራቅ ያለ በመሆኑ ለትራንስፖርት የሚሆን አቅም በማጣቸው ትምህርቱን እንዳቋረጠ በሀዘን ይናገራሉ።

በአዲስ አበባም በተመሳሳይ ተማሪዎች ወላጆቻቸውን ለመደጎም በተለያዩ ስራዎች በመሰማራታቸው ወደትምህርታቸው እንዳልተመለሱ የነገረችን ደግሞ በኮከበ ጽበሃ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነቸው ስንዱ ተፈራ ናት።

ይህ ብቻ አይደለም፣ ወደ ትምህርት ቤት መመለስ የቻሉት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው በመቆየታቸው ትምህርቱን የመርሳት፣ ሀሳባቸውን የመሰብሰብ እና በአግባቡ ትምህርት የመቀበል ችግር እንደገጠማቸው ስንዱ ትገልፃለች።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ወች ባለፈው አመት ባወጣው ሪፖርት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአፍሪካ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ በኃላ ህፃናት ትምህርት እንዳላገኙ ግልፆ ነበር። በርቀት ለማስተማር በተደረገው ሙከራ ተማሪዎች ያገኙት እውቀት እጅግ አነስተኛ እንደሆነም አስታውቋል።

እህቶቿን ጨምሮ በቅርብ ያሉ ቤተሰቦቿ በገጠር እንደሚኖሩ የምትናገረው ስንዱ ኮሮና በተለይ ለሴት ተማሪዎች ይበልጥ ከባድ እንደነበር ትናገራለች።

የባህርዳር ነዋሪ የሆነችው አልማዝ ለጊዜው ጎረቤቶቿ በነፃ እንድትጠቀም የፈቀዱላትን ኤሌክትሪክ ተጠቅማ ከምትሸጠው የድንች ጥብስ በምታገኘው ገቢ ሴት ልጇን ወደ ትምህርት ቤት እየላከቻት ቢሆንም የእሷም ወጪ መሸፈን ካልቻለች እንደ መጀመሪያ ልጇ ትምህርቷን ልታቋርጥ ትችላለች የሚል ስጋት አላት።

XS
SM
MD
LG