በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦፌኮ 'በአንድ ዓመት ውስጥ ምርጫ ይካሄድ' ይላል


OFC
OFC

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ ትናንት ባወጣው መግለጫ "ሁሉን አካታች የጋራ መንግሥት እንዲቋቋምና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ" ሲል ገልጿል። የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና "ሁሉን አካታች ብሔራዊ የመግባባት ድርድር መደረግ አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮምያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ "ኦፌኮ ያወጣው መግለጫ ህዝቡን መሳደብ ይመስላል" ብለዋል። አቶ ታዬ "ድርድር ከዚህ ቀደምም ሲካሄድ ነበር፣ አሁንም ይካሄዳል። በድጋሚ የማካሄድ ምርጫ ግን የለም" ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ኦፌኮ በኢትዮጵያ ሰሞኑን የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት የለውም ማለቱን ተከትሎ ከምርጫ ቦርድ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦፌኮ 'በአንድ ዓመት ውስጥ ምርጫ ይካሄድ' ይላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:33 0:00


XS
SM
MD
LG