በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢዜማ አራት መቶ አቤቱታዎችን አስገብቷል


አበበ አካሉ፣ አንዷለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ አመራሮች
አበበ አካሉ፣ አንዷለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ አመራሮች

በኢትዮጵያ የተካሔደው ምርጫ አጠቃላይ ሂደት መስፈርቱን ያሟላ እንዳልሆነ ኢዜማ ገለፀ። ምርጫ በብዙ ችግሮች ታጅቦ መካሔዱን ያስታወቀው ፓርቲው፣ ከ400 በላይ አቤቱታዎችን ለቦርዱ ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ቦርዱ ለቅሬታዎቹ ምላሽ ካልሰጠ ክስ እንደሚመሰርትም ኢዜማ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ አሁን ላይ ምላሽ የሚሰጠው በድምጽ መስጫው ዕለት ለነበሩ ጉዳዮች መሆኑን እና ኢዜማ ቅሬታ ካለበት ወደ ሚመለከተው የሕግ አካል መሔድ እንደሚችል ገልጿል፡፡

ሰኔ 14 የተደረገውን የ6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ-ኢዜማ፣ ምርጫው በበብዙ ችግሮች የታጀበ ነበር ብሏል፡፡

የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ ፓርቲው በተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙትን ተግዳሮቲች በተመለከተ ከ400 በላይ አቤቱታዎችን ፓርቲው ለቦርዱ ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢዜማ አራት መቶ አቤቱታዎችን አስገብቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00


XS
SM
MD
LG