በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሲቪሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ የአየር ድብደባ መፈጸሙን እማኞች ተናገሩ


ቶጎጓ ዕዳጋ ሰሉስ በምትባል መንደር፤ በሲቪሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ የአየር ድብደባ መፈጸሙን እማኞች ተናገሩ
ቶጎጓ ዕዳጋ ሰሉስ በምትባል መንደር፤ በሲቪሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ የአየር ድብደባ መፈጸሙን እማኞች ተናገሩ

ከመቀሌ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ በምትገኝ ቶጎጓ ዕዳጋ ሰሉስ በምትባል መንደር ደረሰ በተባለ የአውሮፕላን ጥቃት ለገበያ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ ጉዳት እንደደረሰበት ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ተናገሩ።

የዐይን ምስክሮች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና እንዳይገቡ አንቡላንሶች እንዳያልፉ በወታደሮች ተከልክለዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በታጣቂዎች ላይ እንጂ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አልተፈፀመም ብለዋል።

በሌላም በኩል በትግራይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ለሁለት ሳምንት በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ስትዘግብ የቆየችው የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሄዘር መርዶክ በኢትዮጵያ ከቀናት በፊት የተካሄደውን ምርጫ ለመዘገብ ከምትገኝበት አዲስ አበባ ሆና በትግራይ ውስጥ ስለደረሰው ጥቃት ያገኘችውን መረጃ አጋርታናለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሲቪሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ የአየር ድብደባ መፈጸሙን እማኞች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:36 0:00


XS
SM
MD
LG