በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የኢትዮጵያ ስርዓት የሚፈተሽበት ነው - ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ


ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ - በግሪንስቦሮ የሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህር
ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ - በግሪንስቦሮ የሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህር

ኢትዮጵያ ውስጥ ለ6ኛው አጠቃላይ ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚደረገው ዝግጅት ተጠናቆ ነዋሪዎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ባልደረባችን ስመኝኝ የቆየም በግሪንስቦሮ የሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ጋር ደውላ “ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያውያን ምን ትርጉም ይኖረዋል?” ስትል ጠይቃለች።

6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የኢትዮጵያ ስርዓት የሚፈተሽበት ነው - ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:30 0:00

(ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

ፕሮፌሰር ብሩክ አቴንስ ኦሃዮ በሚገኘው ስክሪፕስ የኮምዩኒኬሽንስ ኮሌጅ የጋዜጠኛነት መምህርም ናቸው። በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ አመራር ማዕከል ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል። ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮችና ተልዕኮዎችም ወክለው ያገለገሉ ዲፕሎማትም ናቸው። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ስድስተኛ ሃገራዊ ምርጫ ታዲያ እንደ ማንኛውም ተራ ምርጫ አድርገው እንደማይቆጥሩት ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ከሚከናወነው ምርጫ አስቀድሞ፤ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት፣ መፈናቅል፣ጦርነት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እስር ተከስቷል። በተጨማሪም በፀጥታና በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫየማይካሄድባቸው እና ለመጨው ሳምንት የተላለፈባቸውም አካባቢዎችም አሉ። ፕሮፌሰር ብሩክን - በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚከናወን ምርጫ እንዴት የተሟላ መሆን ይቻላል የሚል ጥያቄ አንስተንላቸዋል።

ይህ ስድስተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ የኢትዮጵያ ስርዓት የሚፈተሽበት ነው የሚሉት ፕሮፌሰር ብሩክ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የተሰተዋሉትን ግጭቶች ጨምሮ ሌላ ተጨማሪ ሁከት ተከስቶ ሰላማዊ ሰዎች የጉዳት ሰለባ እንዳይሆኑ የምርጫውን ውጤት በፀጋ በመቀበል እና ቅሬታዎችን በአግባቡ በማቅረብ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ።

ፕሮፌሰር ብሩክ አክለው፣ ከምርጫው በኋላ ለሚሆነው ነገር ሁሉ ሕዝብም፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና ሀገሪቱንእያስተዳደረ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

በመላ ሀገሪቱ እየተደረገ ላለው ምርጫ ድምፅ ለመስጠት 37 ሚሊዮን ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 167 የሀገር ውስጥ ሲቪክ ማህበራትና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫውን እንደታዘቡ የኢትዮጵያብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በፀጥታ እና በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው በማይካሄድባቸው 59 የምርጫ ክልሎች ደግሞ ምርጫው ጷግሜ 1 ቀን እንደሚካሄድ ቦርዱ ማስታውቁ ይታወሳል::

XS
SM
MD
LG