በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ስለኢትዮጵያ ምርጫ መልዕክት አስተላለፉ


ፎቶ ፋይል፦ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ
ፎቶ ፋይል፦ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ

“መራጮች ሁሉ ድምፃቸውን በነፃነትና በሰላማዊ ሁኔታ መስጠት መቻላቸውን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት፣ የፖለቲካ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው እንዲያረጋግጡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሰኔ 14 ከምታካሂደው ምርጫ በፊት አሳስባለሁ” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጥሪ አሰምተዋል።

ከዋና ፀሃፊው ቃል አቀባይ ቢሮ የወጣው መግለጫ ምርጫው የሚካሄደው ፈታኝ በሆኑ የፖለቲካ፣ የፀጥታና የደኅንነት ሁኔታዎች ውስጥ መሆኑን ዋና ፀሃፊው መጠቆማቸውን አመልክቷል።

“በጉዳዩ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሁሉ ከሁከትና ሁከትን ከማነሳሳት አድራጎቶች ሁሉ እንዲቆጠቡ” ዋና ፀሃፊው ጥሪ ማስተላለፋቸውን መግለጫው ተናግሮ “ምርጫው ውስጥ ያሉ መሪዎችና ተሳታፊዎች ሁሉ ማኅበራዊ አብሮነትን እንዲያራምዱና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያስወግዱ እንደሚያበረታቱ”ም ገልጿል።

ከምርጫው ጋር የተያያዙ ማንኛቸውም ውዝግቦች በንግግርና በተደነገጉት የህግ መሥመሮች ብቻ እንዲፈቱም ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ በአፅንዖት ጠይቀዋል።

ለዚህና ለሌሎችም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ስለኢትዮጵያ ምርጫ መልዕክት አስተላለፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:09 0:00


XS
SM
MD
LG