በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በቦሳሶ


MIGRANTS AT SEA
MIGRANTS AT SEA

በኢትዮጵያዊያ 41 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከ15 ዓመት እድሜ በታች ሲሆን ከ28 በመቶው ደግሞ ከ 15 እስከ 29 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የወጣት ስራአጦች ቁጥር ከ 27 በመቶ በላይ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በዚህ የተነሳም አብዛኞቹ ወጣቶች ምንም ሳይዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን በማቋረጥ በተለያዩ ሃገራት የስራ ዕድል ፍለጋ ይጓዛሉ፡፡

ይሁንና በመንገዳቸው ላይ ካሰቡበት ሳይደርሱ ለብዙ መከራ እና ችግር ይጋለጣሉ፡፡ ወደኋላ ለመመለስም ወደፊት ለመሄድም አጥብቂኝ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ከሳምንት በፊትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በፑንትላንድ ሶማሌ ቦሳሶ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም IOM በኩል ለመመለስ መወሰናቸውን ተሰምቷል፡፡

የ19 ዓመቱ ኑሩሰዒድ አደም ከደቡብ ወሎ ሲነሳ በኪሱ የያዛት 200 ብርብቻ እንደሆነች ይናገራል፡፡ ደላላው ለመንገድ ብሎ ከሰጠው 500 ብር ጋር 800 ብር ሆነልኝ ይላል፡፡ የኢትዮጵያን ድንበር እስኪያልፉ ድረስ መልካም የነበሩት ደላሎች ግን ሕይወታቸውን በአንዴ ወደ ስቃይ ለወጡባቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ወደ ሃገሩ ለመመለስ በመወስን በሌሊት ጠፍቶ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ተቋም IOM ውስጥ በመግባት እራሱን አትርፏል፡፡ በተመሳሳይ ሉባባ ሰዒድም ከቤቷ ስትወጣ የለበሰቻትን ብቻ እና የተሻለ ሕይወት ተስፋን ሰንቃ ነበር፡፡ በበረሃ ውስጥም ረሃብ፣ ጥም፣ ድካም ተፈራርቀውባታል፡፡ ከሁሉ የሚያስፈራት የነበረው በበረሃው ውስጥ እየደከሙ ወድቀው የሚቀሩት ወጣቶች እና የደላሎቹ ሴቶችን እንዳሻቸው መድፈር ነበር ትናገራለች፡፡ ፡እንደ ዕድል ሆኖም ከወራት በኋላ ከደላላው እጅ አምልጣለች፡፡

በቦሳሶ የሚገኘው ወጣት እና ከአሪሲ የተነሳው ወጣት ፍልሰተኛ ኢብራሂም አደምም ደላሎቹ አስረው እየገረፉ ከወላጆቹ ብር እንደተቀበሉ የስቃይ ህይወቱን ይተርካል፡፡ በአሁን ሰዓት በሶማሊያ ቦሳሶ ለመመለስ ከወሰኑት ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን በዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ተቋም IOM ካምፕ ውስጥ ይገኛል፡፡

ኤደን ገረመው እነዚህን ወጣቶችና በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ተቋም IOM ውስጥ የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ብሔራዊ መርሃግብር አባል የሆኑትን እስከዳር ጤናዬን አነጋገራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በቦሳሶ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:44 0:00


XS
SM
MD
LG