በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀረጥና የግብር ቅናሽ ከተደረገለት በኋላ ዋጋው በእጥፍ የጨመረው የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ


“ሴት እህቶቻችን የንጽህና መጠበቂያ አጥተው ኩበት ይጠቀማሉ” ትላለች የጀግኒት ኢትዮጵያ መስራች እና አስተባባሪ ማራኪ ተስፋዬ፡፡

በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው የወር አበባ ለማየት ከደረሱ ሴቶች ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት በቂ የሆነ ወርሃዊ የንጽህና መጠበቂያ እንደሌላቸው በቅርብ ጊዜ የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ሁኔታውን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆኑት ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት የሚያስችል አቅም የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ሴቶች የንጽህና መጠብቂያዎችን በቀላሉ እንዲገኙ ለማስቻል የሚረዳ የቀረጥ እና የታክስ ማሻሻያ ማድረጉን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚንስቴር ቢገልጽም የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ዋጋ ግን ባለፉት 6 ወራት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ በዚህ ዙሪያ የገንዘብ ሚኒስቴርን፣ የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ባለስልጣንን፣ የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተስፋ ለኢትዮጵያ የሸማቾች ማኅበርን፣ የጀግኒት ኢትዮጵያ ንቅናቄን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን አነጋግረናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የቀረጥና የግብር ቅናሽ ከተደረገለት በኋላ ዋጋው በእጥፍ የጨመረው የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00


XS
SM
MD
LG