በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በተመድ የቻይና ተፅዕኖ ላይ አትኩራለች


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ

ዩናይትድ ስቴትስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቻይና ተጽዕኖ ላይ አትኩራለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ትናንት ረቡዕ ዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ፊት ቀርበው በሰጡት ቃል ቻይና በዓለሙ ድርጅት የያዘችው "የተንኮል ተጽዕኖ እንቅስቃሴ" ሲሉ የጠሩትን፣ እየተከታተልኩ ለመግታት እየሰራሁ ነኝ ሲሉ አስታወቁ።

ቤጂንግ የአለሙን ማኅበረሰብ ህብረ ብሄራዊነት የሚቀናቀን አምባገነናዊ መንገድ እየተከተለች ነች ሲሉም አምባሳደር ግሪንፊልድ አሳስበው፣ ተጽዕኖዋን ለማስፋት ለያዘችው ተግባር ማሳያ ሦስት የመንግሥታቱ ድርጅት ቴክኒካዊ መስሪያ ቤቶች የሚመሩት በቻይናውያን መሆኑን ግለጸዋል፤ የኮቪዲ-19 ክትባት ዲፕሎማሲ ላይ ተሰማርታ አንዳንዶቹን ደሆች ሃገሮችን ልትጫን እየሞከረች ትገኛለች። የምታደርገውን ጥረት ለማስቆም ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።

አያይዘውም የዩናይትድ ስቴትስ የተመድ ቋሚ መልዕክተኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት በድርጅቱ ባለፈው የትረምፕ አስተዳደር ዘመን ያሽቆለቆለውን የዩናይትድ ስቴትስን ተደማጭነት ለመመለስ አስፈላጊውን መዋዕለ ነዋይ እንዲመድቡ ጥሪ አሰምተዋል።

“ጠላቶቻችን እና ተፎካካሪዎቻችን እያደረጉ ነው። እኛም ያን ሳናደርግ ልንፎካከር አንችልም" ብለዋል።

አራት ሰዓት በፈጀው የምስክር ቃል ሰሚ ሸንጎ የታደሙት ለአርባ የሚበልጡ የምክር ቤት አባላት እንጋፋይቱን ዲፕሎማት በመንግሥታቱ ድርጅት የባይደን አስተዳደርን ቅድሚያ ትኩረቶች የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች አቅርበውላቸዋል።

XS
SM
MD
LG