በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውሳኔና የኢትዮጵያ ምላሽ


ታላቁ የኅዳሴ ግድብ
ታላቁ የኅዳሴ ግድብ

የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ታላቁን የኅዳሴ ግድብ በተመለከተ ኳታር፤ ዶሃ ላይ ያሳለፉት ውሳኔን ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ17ቱ አረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያሳለፉት ውሳኔ ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሊጉ አባል ሀገራት በዶሃው ስብሰባቸው የታላቁን የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ለመፍታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።

ይህን ተከትሎ የአረብ ሊግ በግድቡ ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም መያዙ የመጀመሪያው አይደለም ያለው መግለጫው የኅዳሴውን ግድብ ዓለማቀፋዊ እና የፖለቲካ አንድምታ እንዲኖረው ማድረግ በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብር እና በዘላቂነት ወደ መጠቀም አይመራም ብሏል።

ሊጉ ለግብፅ እና ሱዳን መሠረተ ቢስ የይገባኛል ጥያቄ የጎላ ድጋፍ የተነሳ በግድቡ ዙሪያ ገንቢ ሚና የመጫወት ዕድሉን አስቀድሞ አባክኖታል ያለው የኢትይጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫው የአባይን ውሃ አልምቶ መጠቀም ለኢትዮጵያም የህልውና ጉዳይ መሆኑን የአረብ ሊግ ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

አባይ የጋራ ሀብት እንጂ የግብጽ እና ሱዳን የተናጠል ንብረት አለመሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ የአባል ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ደኅንነት ሊረጋገጥ የሚችለው በትብብር እና በውይይት ብቻ መሆኑን ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች ብሏል በመግለጫው፡፡

የአረብ ሊግ የአባይ ተፋሰስ የሆኑ ሌሎች ሀገራትን ወደ ጎን በመተው ለሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ብቻ ማድላቱ የተሳሳተ አካሄዱ ማሳያ ነው፡፡

ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ይሞላል ያለው መግለጫው፤ የግድቡን አሞላል በተመለከተ ሊጉ የያዘውን አቋም የኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG