በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣዩ ምርጫ ላይ


የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ አምቦ ከተማ ውስጥ
የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ አምቦ ከተማ ውስጥ

ብልፅግና ፓርቲ ከተመረጠ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ፣ በምጣኔ ኃብትና ሥርዓትን በመገንባት ላይ እንሠራለን" ሲሉ የፓርቲው የኦሮምያ ክልል ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ፓርቲያቸው ዛሬ አምቦ ውስጥ ባካሄደው ቅስቀሳ ላይ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል “የማስመሰል” ባለው ምርጫ ውስጥ ኦነግ ባለመሳተፉ አለመፀፀቱን የተናገሩት በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ የህዝብ ግንኙነት ጊዜያዊ ኃላፊ ፓርቲያቸው “ምርጫ ውስጥ ባይሳተፍም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የጀመረውን ተሣትፎ በሰላማዊ መንገድ ይቀጥላል" ብለዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ ኦፌኮ/ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ደግሞ "ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ኦሮምያ ውስጥ ብቻውን በመወዳደሩ የአገሪቱን ችግር ከማባባስ ውጭ የሚያገኘው ትርፍ ይኖራል ብለን አንጠብቅም" ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣዩ ምርጫ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00


XS
SM
MD
LG