በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ትዊተርን ከሀገሯ ማገዷን ዩናይትድ ስቴትስ አወገዘች


የማኅበራዊ መገናኛው ትዊተር የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሞሃማዱ ቡሃሪ በገጻቸው ያሰፈሩትን ጽሁፍ ማንሳቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ የናይጄሪያ መንግሥት የወሰደው እርምጃ በዲሞክራሲ ሥርዓት ቦታ የለውም በማለት አውግዛዋለች።

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ ናይጄሪያ ዕገዳዋን እንድትሰርዝ ጠይቀዋል፣ የመናገር ነጻነት እና በኢንተርኔት መረብም ሆነ በሌሎቹ መንገዶች የመረጃ ተደራሽነት ለአንድ ሃገር ብልጽግና እና ዲሞክራሲ መሰረቱ ናቸው ብለዋል።

የናይጄሪያ መንግሥት በትዊተር ላይ የወሰደውን እርምጃ እና በማኅበራዊ መገኛኛው ሲጠቀሙ የሚገኙ ናይጄሪያውያን ይታሰራሉ፣ ይከሰሳሉ ብሎ ማስፈራራቱን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታወግዝ ኔድ ፕራይስ አሳስበዋል። በተጨማሪም የናይጄሪያ የቴሌቭዥን እና ራዲዮ ሥርጭት ኮሚሽን ጋዜጠኞች በትዊተር እንዳይጠቀሙ ትዕዛዝ መስጠቱ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳሰበ አድራጎት ነው ብለዋል።

ከአሁኑ ቀደምም ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከአውሮፓ ህበረት፣ ከብሪታንያ፣ ከአየርላንድ እና ከካናዳ ጋር ሆና የናይጄሪያን እርምጃ እንዳወገዘች ይታወሳል።

የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ቡሃሪ በቅርቡ የተካሄዱ አመጾች ተሳታፊዎችን ለማስጠንቀቅ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩትን ቃል የዩናይትድ ስቴትሱ የማኅበራዊ መገናኝ ኩባኒያ አንስቶታል፥ ቡሃሪ በደቡቡ የሀገሪቱ ክፍል "ጸባይ የጎደለው ሁከት የምትፈጽሙ ከአርባ ዓመት በፊት የነበረውን የእርስ በርስ ብጥብጥ የማታውቁ ናችሁ። እኛ ለሠላሳ ወራት ውጊያ አምባ ውስጥ የነበርነው በሚገባችሁ ቋንቋ እንነግራችኋለን ሲሉ ጸፈዋል፥ ትዊተር ደንቦቼን የጣሰ ጽሁፍ ነው ብሎ ከሰረዘባቸው በኋላ የናይጄሪያው መንግሥት ላልተወሰነ ጊዜ ዘግቶታል።

XS
SM
MD
LG