በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል ተጠርጣሪዎችን አሳልፋ እንድትሰጥ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ ፋቱ ቤንሱዳ
ፎቶ ፋይል፦ ፋቱ ቤንሱዳ

አይሲሲ ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል በመፈጸም ተጠርጣሪዎችን አሳልፋ እንድትሰጠው ጠየቀ። የሱዳን መንግሥት ዳርፉር ውስጥ የጦር ወንጀል በመፈጸም የተወነጀሉ አራት ተጠርጣሪዎችን ለሄጉ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት እንድትሰጥ ተሰናባቿ የፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ጠየቁ።

ፋቱ ቤንሱዳ ትናንት ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ባደረጉት በፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ህግነት የመጨረሻቸው በሆነው ገለፃቸው የሱዳን መንግሥት አዲሲቱ ሱዳን በወንጀል አለመጠየቅን በመዋጋት ለፍትህ እና ለህግ የበላይነት መከበር በመቆም ሙሉ በሙሉ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር መቀላቀሏን በተጨባጭ ማሳየት አለበት ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹ በሙሉ በሱዳን መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስለሆኑ ለፍርድ ቤቱ አሳልፎ ለመላክ የሚከለክል እንቅፋት የለም ብለዋል አቃቤ ህጓ።

እስካሁን በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቁጥጥር ሥር የዋለው አሊ ኹሳይብ በሚል ስም የሚጠራው እና ከአንድ ዓመት በፊት እጁን የሰጠው የወንጀሉ ተጠርጣሪ ብቻ ነው።

ጋምቢያዊቱ ፋቱ ቤንሱዳ በሚቀጥለው ሳምንት ከስራቸው የሚሰናበቱ ሲሆን እንግሊዛዊው የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ካሪም ኻን ይተኳቸዋል።

XS
SM
MD
LG