በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሜሩን ውስጥ የሚካሄደው ግጭት እና የአሜሪካ ቪዛ ዕገዳ


በካሜሩን መንግሥት ሃይሎች እና በእንግሊዝኛ ተናግሪው የሀገሪቱ ክፍል በሚንቀሳቀሱት አማጽያን መካከል የሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊቱዋን እያጠናከረች የምትገኘው ዩናይትድ ስቴትስ ቀውሱን ለማክተም የሚደረገው ጥረት እንዳይሳካ የሚያደርጉ በተባሉ ግለሰቦች ላይ የቪዛ ዕገዳ ጥላለች።

ሁለቱ የካሜሩን እንግሊዝኛ ተናጋሪ ክፍል ግዛቶች በአብዛኛው ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ከሆነው የሀገሪቱ መንግሥት ለመገንጠል እአአ ከ2017 ጀምረው በሚያካሂዱት ውጊያ እየታመሱ ሲሆን ከ3,500 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ ከ700,000 የሚበልጡም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ብጥብጡ ዩናይትድ ስቴትስን በእጅጉ እያሳሰባት መሆኑን ገልጸው ሁለቱም ወገኖች ድርድር እንዲያካሂዱ አሳስበዋል።

የቪዛ ክልከላው ቀውሱ በሰላማዊ መንገድ እንዲያከትም እና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ያለንን አቋም የሚያንጸባርቅ ነው ሲሉ የቪዛ ክልከላው የሚመለከታቸውን ግለሰቦች አልጠቀሱም።

የመብት ድርጅቶች ሁለቱንም ወገኖች የጭካኔ አድራጎት በመፈጸም ይከሳሉ።

XS
SM
MD
LG