በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ፎቶ ፋይል፦ ህንድ
ፎቶ ፋይል፦ ህንድ

ህንድ በዛሬው ዕለት 100,636 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች መመዝገባቸውን አስታወቀች። ቁጥሩ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በአንድ ቀን ይገኙ ከነበሩት ሁሉ ዝቅተኛው መሆኑን ገልጻለች ፥ በሃያ አራት ሰዐት ጊዜ ውስት 2,427 ስዎች እንደሞቱም አክላ አስታውቃለች

በሌላ ዜና የብሪታንያ የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ ትናንት ዕሁድ በሰጡት ቃል መጀመሪያ ላይ ህንድ ውስጥ የተገኘውና አሁን ዴልታ በሚል ስም የሚጠራው የኮሮናቫይረስ ዓይነት እንግሊዝ ውስጥ ከተገኘው አልፋ ከተባለው ዝርያ በአርባ ከመቶ ይበልጥ ፍጥነት ሳይተላለፍ አይቀርም ሲሉ ተናገሩ።

እንግሊዝ ውስጥ በፍጥነት ሲዘመት የነበረው መጀመሪያ ላይ ከኬንት ክፍለ ሃገሯ የተቀሰቀሰው አልፋው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ሲሆን አሁን ግን የዴልታው ዝርያ በይበልጥ እየተዛመተ መሆኑን ነው የጤና ሚኒስትሩ የተናገሩት።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል ባለው አሃዝ መሰረት ከብሪታንያ ህዝብ አርባ ከመቶው ሙሉ በሙሉ መከላከያ ክትባቱን የወሰደ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም የአዲስ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልጆች የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ አለባቸው ሲሉ የቢይለር ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ቤት ድሬክተር አሳሰቡ።

ዶ/ር ሪቺና ብሴት ለሲ ኤን ኤን ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅ "አዋቂዎች እየተከተቡ ሲሄዱ ቫይረሱ ማህበረሰቡ ውስጥ ሌላ የሚጠጋው አካል መፈለጉ አይቀርም ፥ በመሆኑም ልጆች ይጋለጣሉ" ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 173 ነጥብ 3 ሚሊዮን የገባ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ 33 ነጥብ 3 ሚሊዮኑን ይዛ ቁንጮው ላይ ስትሆን ህንድ 29 ሚሊዮን ብራዚል 17 ሚሊዮን ይዘዋል።

XS
SM
MD
LG