በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጄነራል ሰአረ ግድያ ብይን ተሰጠ


በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰአረ መኮንንና በሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ በተከሰሱት የአሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ላይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ብይን ሰጥቷል።

በኤታ ማዦር ሹሙና በሜጀር ጄነራል አበራ ላይ ሰኔ 15 / 2011 ዓ.ም. ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ በአሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ላይ የተመሠረተውን ክስ ሲመረምር የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሹ ላይ የጥፋተኛነት ብይኑን ያሳለፈው በተሰየሙት ዳኞች ሙሉ ድምፅ እንደሆነ ታውቋል።

የተከሳሹ ጠበቃ ቃለ ክርስቶስ ጌትነት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃል ደምበኛቸው የተከሰሱት ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመለወጥ ወንጀል ፈጽሟል በሚል እንደሆነ ጠቁመው ከ2ኛ እስከ 13ኛ የነበሩትን ክሦች መንግሥት ቀደም ሲል አንስቶ የአሥር አለቃ መሳፍንት ግን መቀጠሉን ገልፀዋል።

በምርመራና የክስ ሂደቱ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠበቃ ቃለ ክርስቶስ ገልጸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለሰኔ 11/ 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን የተከሳሹ ጠበቆች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በጄነራል ሰአረ ግድያ ብይን ተሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00


XS
SM
MD
LG