አምቦ —
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ኮቪድ-19 ምርመራ ማእከል ከሚያደርጋቸው ምርመራ መካከል ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት በወረርሽኙ መያዛቸን እንደሚያመለክት ማዕከሉ አስታወቀ።
በሌላ በኩል የጉደር ሆስፒታል ኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ውስጥ ከነበሩ ታካሚዎች ከአንዱ ውጭ ሌሎቹ ተሽሏቸው እንደወጡ የማዕከሉ አስተባባሪ አስታቀዋል።
ሁለቱም አስተባባሪዎች የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት አሁንም ጥንቃቄው መቀጠል አለበት ብለዋል።
ከበሽታው ድነው ወደ ቤታቸው የተመለሱ አንድ የአምቦ ከተማ ነዋሪም ኮቪድ-19 አስከፊ በሽታ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዳይለየው እመክራለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡