በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት እና የጃፓን ኦሎምፒክስ


የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለዓለም ባለ ዝቅተኛ ገቢ ሃገሮች እንዲዳረስ የሚሰራው በዓለም የጤና ድርጅት መሪነት የተዋቀረው ስብስብ ኮቫክስ ግዙፍ የገንዘብ ድጋፍ አገኘ።

ጃፓን ትናንት ረቡዕ በኢንተርኔት አማካይነት ባስተናገደችው የመሪዎች ጉባዔ ላይ ኮቫክስ የሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ቃል የተገባለት ሲሆን ከሁሉም ትልቁ የሆነውን ድጋፍ እንደምትሰጥ ያስታወቀችው አስተናጋጅቱ ሃገር ጃፓን ስምንት ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ብላለች።

ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔይን እና ስዊድን ከፍ ያለ የገንዘብ እርዳታ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል። ኮቫክስ ከተቋቋመ ወዲህ እስካሁን ዘጠኝ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር አሰባስቧል።

በርካታ ሃገሮች ካከማቹት የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ክትባት ውስጥ የተወሰነውን ለኮቫክስ ሊለግሱ ቃል የገቡ ሲሆን በዚህም ጃፓን ከሁሉም ትልቁ የሆነውን ሰላሳ ሚሊዮን ክትባቶች እንደምትለግስ ቃል ገብታለች።

በመሪዎች ጉባዔው ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሃሪስ ባሰሙት ንግግር የባይደን አስተዳደር በያዝነው ዓመት እና በሚመጣው የእአአ 2022 ውስጥ ለኮቫክስ የሚሰጥ 4 ቢሊዮን መመደቡን ጉባኤተኞቹን አስታውሰዋል። ሌላ አዲስ የገንዘብም ሆነ የክትባት ድጋፍ ቃል አልገቡም። ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ ካላት የኮቪድ ክትባት ክምችት ሰማኒያ ሚሊዮን ክትባቶች እንደምትሰጥ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚክፈተው ውዝግብ የተደራረበት የቶኪዮ የበጋ ኦሊምፒክስ በዚህ ሳምንትም አዲስ እክል ገጥሞታል።

በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለው የኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት አስር ሽህ የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ሰራተኞች ስራቸውን ለቀዋል።

የቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ውድድሩ ላይ የውጭ ሃገር ታዳሚዎች እንዳይገኙ የተከለከለ በመሆኑ የበጎ ፈቃደኞቹ ሥራ መልቀቅ ችግር አያመጣም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG