በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት ለታዳጊዎች


የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት አምራች ኩባኒያ ሞደርና አስራ ስምንት እና ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ ለሆኑ ለሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባቱ የፌዴራል መንግሥቱ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ሙሉ ፈቃድ እንዲሰጥ ጠየቀ።

በሁለት ጊዜ የሚሰጠው የሞደርናው ክትባት የምድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደሩ ሥራ ላይ እንዲውሉ ፈቃድ ከሰጣቸው ሦስት ክትባቶች አንዱ ሲሆን በሀገሪቱ ዙሪያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ እንዲቀንስ ትልቅ አስተዋጻዖ አድርጓል።

ሞደርና ባለፈው ታህሳስ ወር በአጣዳፊ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃዱን ካገኘ ውዲህ አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ክትባቶችን በሃገሪቱ ዙሪያ አከፋፍሏል። አሁንም ክትባቱ ከአስራ ሁለት እስከ አስራ ሰባት ዓመት ለሁኑ ወጣቶች ቢሰጥ እንደማይጎዳ እና ቫይረሱን እንደሚከላከል በመታወቁ ተጨማሪ ፈቃድ እንዲሰጠው አመልክቷል። የፋይዘሩ ክትባት ባለፈው ወር ለታዳጊ ወጣቶች እንዲሰጥ በቅርቡ ፈቃድ አግኝቷል።

XS
SM
MD
LG