ዋሺንግተን ዲሲ —
በአውስትራሊያዋ ደቡባዊ ቪክቶሪያ ክፍለ ሃገር ውስጥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ታውጆ የነበረውን የአንድ ሳምንት የእንቅስቃሴ ክልከላ በዋና ከተማዋ ሜልበርን እንዲራዘም ተወስኗል።
የእንቅስቃሴ ክልከላው የታወጀው በቪክቶሪያ ዙሪያ በፍጥነት የሚዛመተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ መታየቱን ተከትሎ ነበር። ዛሬ በክፍለ ሃገርዋ ስድስት አዲስ የቫይረሱ ተጋላጮች የተገኙ ሲሆን በጠቅላላው የተረጋገጠው ቁጥር ስድሳ መድረሱን ነው ባለስልጣናቱ ይፋ ያደረጉት።
የቪክቶሪያ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትር ጄምስ ሜርሊኖ መልበርን ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ይህን ነገር መደምሰስ አለብን አለበለዚያ ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል ብለዋል።