በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግዙፉ የሥጋ ማምረቻ ድርጅት የኮምፒውተር ሰርጎ ገብ ጥቃት ደረሰበት


"ጄቢኤስ" የተሰኘውና በዓለም ላይ ግዙፉ የሥጋ ማምረቻ ድርጅት በደረሰበት የኮምፒውተር ሰርጎ ገብ ጥቃት በአውስትራሊያና በሰሜን አሜሪካ የሚገኘውን ምርቱን ማቆሙን ትናንት አስታውቋል። የድርጅቱ አመራሮች ችግሩን ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የሚደጎመው ጄቢኤስ ትናንት ባወጣው መረጃ ጥቃት እንደደረሰ፣ በጥቃቱ የተጎዱትን ስርዓቶች ሥራ እንዲያቆም ማድረጉን፣ የሚመለከታቸውን ባለሥልጣናትን ማሳወቁን እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የድርጅቱ የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ችግሩን እንዲፈቱ ማሳወቁን እንደገለፀ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።

በዚህም ምክንያት ከተጠቃሚዎችና ከጥሬ እቃ አቅራቢዎች ጋር ያለው የንግድ ውል እንደሚዘገይ የድርጅቱ መግለጫ ጨምሮ ገልጿል።

እስካሁን የደምበኞችና የአቅራቢዎች እንዲሁም የሰራተኞች የግል መረጃ አደጋ ላይ ይውደቅ፣ አይውደቅ አልታወቀም። ሆኖም የድርጅቱ መጠባበቂያ የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓት ግን

'የተቀነባበረ የኮምፒውተር ጥቃት' በተባለው አደጋ እንዳልተጎዳ ድርጁት ጨምሮ ገልጿል።

ለዓለም ገበያ ሥጋ በማቅረብ ትልቁ የሆነው ይህ ድርጅት በካናዳ፣ ብሪታኒያ፣ አውሮፕ፣ ኒው ዚላንድ እና ሜክሲኮ የሚንቀሳቀስ ነው።

XS
SM
MD
LG