በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴኔተር ጂም ኢንሆፍ በኢትዮጵያ


ሴኔተር ጂም ኢንሆፍ እና ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
ሴኔተር ጂም ኢንሆፍ እና ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሪፐብሊካን ሴኔተር ጂም ኢንሆፍ በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

ሴኔተር ጂም ኢንሆፍ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ማስታወቃቸውን ጠቅሶ የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው

“የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑትን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር፣ ጂም ኢንሆፍን ወደ ሁለተኛው ቤትዎ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ እላለሁ” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሴኔተር ኢንሆፍ ወደኢትዮጵያ የተጓዙት በግል ይሁን በይፋዊ ጉብኝት የዜና አገልግሎቱ ዘገባ በዝርዝር አልገለጸም።

ፋና ብሮድካስት በበኩሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሴናተር ጂም ኢንሆፍን መቀበላቸውን ገልጾ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ዘገባው አክሎም ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ባለፈው ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን የቪዛ እገዳ አስመልከተው

"የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን የቪዛ ዕገዳዎችን እንደሚቃወሙ ማስታወቃቸው እና የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሽብርተኛው ድርጅት ህወሓት ጋር በተመሳሳይ ረድፍ ለማስቀመጥ መሞከር ተቀባይነት የለውም በማለት፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሉንም ሰላማዊ መፍትሔዎችን ለማምጣት እየሰራ ይገኛል፤ ሰላምንና አንድነትን ከማምጣት ውጪ ሌላ አካሄድ አልሄደም” ማለታቸውን አውስቷል።

XS
SM
MD
LG