በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሚሞሪያል ዴይ"


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በግዳጅ ላይ የወደቁ አርበኞች መታሰቢያ "ሚሞሪያል ዴይ" ንግግራቸው ዲሞክራሲ አደጋ ላይ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ።

በሀገር ውስጥም በውጭም ዲሞክራሲ አደጋ ላይ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዛሬው በግዳጅ ላይ የተሰዉ አርበኞች መታሰቢያ በዓል ላይ ባደጉት ንግግር አስጠነቀቁ።

ፕሬዚዳንቱ ከምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሃሪስ እና ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ሆነው በአርሊንግተን መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን ማኖር ሥነ ስራዓት ከአካሄዱ በኋላ ንግግር አድርገዋል።

እአአ ባለፈው ጥር ስድስት ቀን እሳቸው ሪፐብሊካኑን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕን ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለማስቀልበስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ላይ የተፈጸመውን ወረራ በተዘዋዋሪ በጠቀሱበት ንግግራቸው "አሁን የምናደርገው ነገር እንዲሁም የወደቁልንን የምናስብበት መንገድ ዲሞክራሲያችን ወደፊት ጸንቶ መዝለቅ አለመዝለቁን ይወስነዋል" ብለዋል።

በምክር ቤቱ ላይ የተፈጸመውን ወረራ የሚመረምር የሁለቱንም ፓርቲዎች አባላት የያዘ ኮምሽን እንዲቋቋም በተወካዮች ምክር ቤት ያለፈውን ህግ ባለፈው ዓርብ የመወሰኛ ምክር ቤት ሪፐብሊካኖች እንዳያልፍ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG