በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የእንቅስቃሴ ገደቦች ዕወጃ


ፎቶ ፋይል፦ ጆሃንስበርግ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ወደማኖሪያ ሥፍራ ሲጓጓዝ
ፎቶ ፋይል፦ ጆሃንስበርግ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ወደማኖሪያ ሥፍራ ሲጓጓዝ

በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት እየተባባሰ በሚገኝባት በደቡብ አፍሪካ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውሉ አዳዲስ የእንቅስቃሴ ገደቦች ታውጀዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዞደንት ሲሪል ራማፎሳ ዛሬ ከማታው አምስት ሰዓት ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል የሌሊት የሰዓት ዕላፊ አውጀዋል፥ በዚህም መሰረት ምግብ ቤቶች ቡና ቤቶች እና የስፖርት እንቅስቃሴ ማዕከሎች ማታ ከወትሮው በአንድ ሰዓት ቀደም ብለው እንዲዘጉ ተደርጓል። በተጨማሪም ቤት በህዝባዊ ዝግጅቶች ላይ መሰባሰብ የሚችለው ደጅ ከሆነ ሁለት መቶ ሃምሳ፣ ቤት ውስጥ ከሆነ ደግሞ አንድ መቶ ሰው ብቻ እንዲሆን ታውጇል።

ደቡብ አፍሪካ ባለፈው የሃያ አራት ሰኣት ጊዜ 4,515 የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች መገኘታቸውን አውጃለች። ባለፈው የአንድ ሳምንት ጊዜ በአማካዩ በየቀኑ 3,745 እንደተገኙ ተመልክቷል። ክትባቱን በሚመለከት ደግሞ እስካሁን የተከተቡት ከስድሳ ሚሊዮኑ የሀገሪቱ ህዝብ ውስጥ ከአንድ ከመቶ የሚያንስ ቁጥር ያላቸው 963,000 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትሱ የጃንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል ሰንጠረዥ ያሳያል።

XS
SM
MD
LG