በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለቶኪዮ ኦሊምፒክስ ታዳሚዎች መመሪያ


አንድ የጃፓን ጋዜጣ በዘገበው መሰረት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድሮችን ለመመልከት የሚገኙ ታዳሚዎች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰዳቸውን ወይም ተመርምረው ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያሳይ ማረጋገጫ ማሳየት ይኖርባቸዋል።

የጃፓን መንግሥት ባለሥልጣናት በውድድሮቹ ላይ የሚገኙ ተመልካቾች ምግብ መብላት፥ በጩኸት ሆታ ማሰማት ወይም እጅ ለእጅ እየተመታቱ የደስታ ስሜት መለዋወጥ እንዲከለከል እየተነጋገሩ መሆናቸውን ዩሙዊሪ ሺንቡን ጋዜጣ ዘግቧል።

በመላዋ ጃፓን አዲስ የኮቪድ-19 ስርጭት ማዕበል እየተስፋፋ ባለበት እና የክትባቱም ሂደት ዝግተኛ በሆነበት ባሁኑ ወቅት በሀምሌ ወር የሚካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ከህዝቡ በኩል የሚቀርበው ተቃውሞ እየጨመረ መጥቷል።

ዋና ከተማዋ ቶኪዮ እና በርካታ የሃገሪቱ ክፍለ ሀገሮች ላይ የተጣለው እና ዛሬ ሊያበቃ የነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እአአ እስከ ሰኔ ሃይ ተራዝሟል።

XS
SM
MD
LG