በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ በሶማሊላንድ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሶማሊላንድ ውስጥ ምክር ቤታዊ እና የአካባቢ ተወካዮች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ ሰኞ በዋና ከተማዋ ሃርጌሳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን ለመስጠት ማልደው ረጃጅም ሰልፎች ይዘው ሲጠብቁ ታይተዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል በሰጡት ቃል ምርጫው በሰላማዊ መንገድ ይከናወናል ብለን እንጠብቃለን ብለው፤ ቅሬታ የሚኖረው ወገን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ ይችላል፤ ፍርድ ቤቶች ክፍት ናቸው" ብለዋል።

በዚህ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከአንድ ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸው ታውቋል፥ ከሦስት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫ የተመዘገቡት ሰባት መቶ ሽህ ብቻ እንደነበር የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ጠቅሰዋል።

XS
SM
MD
LG