በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኅዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የባቡር መሥመር ፕሮጀክት እክሎች አጋጥመውታል


የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ባቡር ሥራ ፕሮጀክት
የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ባቡር ሥራ ፕሮጀክት

አሁን ባለው ምንዛሬ ከ71.4 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበት የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ባቡር ሥራ ፕሮጀክት የግንባታና መስመር ዝርጋታው ቢጠናቀቅም በኃይል አቅርቦት እጥረት አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አለመጀመር በሚሊዮኖች ብር ለሚገመት ንብረት ብልሽትና ዘረፋ ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል አቅርቦት ስራው የተጓተተው ከመንግሥት በኩል አስፈላጊው ገንዘብ እስኪለቀቅና ከዋስትና ሂደት ጋር በተያያዘ መሆኑን አምኗል፡፡

የኃይል አቅርቦት ስራውን ከሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ ለማካሄድ መታቀዱንም አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከታላቁ ኅዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፍ የተባለለትና ከ71.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደረገበት የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ባቡር ሥራ ፕሮጀክት በሁለት ምዕራፎች ነው እየተሰራ ያለው፡፡

ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለውና 270 ኪ.ሜ የሚረዝመው የመጀመሪያው ምዕራፍ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣ ከኮምቦልቻ እስከ ሃራ ገበያ ወልዲያ ያለው 122 ኪ.ሜ ደግሞ 83 በመቶ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ማኔጀር ኢንጂነር አብዱል ከሪም መሐመድ ገልጸዋል፡፡

በስድስቱ የሰው ማጓጓዣ ባቡሮች ደግሞ በቀን ከ4300 በላይ ሰዎችን ማጓጓዝ ይቻላል እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ፡፡

ሥራው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270ኪ.ሜ በኃይል አቅርቦት እጥረት አገልግሎት ሳይሰጥ ሁለት ዓመታት ተቆጥሯል፡፡

ከኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ወልዲያ ያለውን ደግሞ የሙከራ ተግባር ለመፈጸም አልተቻለም፡፡

ይህ ደግሞ ብዙ የተባለለት ፕሮጀክት በተባለለት ልክ ወደ ሥራ እንዳይገባ እንቅፋት ፈጥሮበታል ይላሉ ኢንጂነር አብዱልከሪም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከኅዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የባቡር መሥመር ፕሮጀክት እክሎች አጋጥመውታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00


XS
SM
MD
LG