በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፖለቲካ መሪዎች ምርጫ ለማካሄድ ሥምምነት ተፈራረሙ


ፎቶ ፋይል፦ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ
ፎቶ ፋይል፦ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ

የሶማሊያ መሪዎች በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ መስማማታቸው ተገለጸ። የፖለቲካ መሪዎቹ ለረጅም ጊዜ የዘገየው የምክር ቤት አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ማቀፍ ዙሪያ በትንናትናው ዕለት ሥምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ሥምምነቱ ሃገሪቱን ወደፖለቲካዊ ብጥብጥ የሚያመራት ቀውስ እንዳይከሰት የሚከላከል እንደሚሆን ተስፋ አድርገዋል።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሮብሌ እና የአምስቱ የክልል መንግሥታት መሪዎች ፊርማቸውን ያኖሩበት ሥምምነት ምክር ቤታዊ ምርጫዎቹን በሁለት ወር ጊዜው ውስጥ የሚቻልበትን ዕቅድ አስቀምጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር መንግሥታቸው ውሉን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የተመድ የሶማሊያ ተወካይ ጄምስ ስዋን በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙትን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተጠሪዎች ወክለው ባሰሙት ንግግር፣ ሶማሊያውያን በመሩት እና ሶማሊያውያን በቀረጹት ሂደት ከዚህ ሥምምነት ላይ በመድረሳቸው አክብሮታችንን እንገልፃለን ብለዋል።

ሥምምነቱ ላይ የተደረሰው ሞቃዲሾ ውስጥ አራት ቀናት የፈጀ የተጋጋለ ድርድር ከተካሄደ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG