በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሰላም ለሁሉም" የሰላም መድረክ


ገዱ አንዳርጋቸው
ገዱ አንዳርጋቸው

በወሎና አካባቢው አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን በጎ ተፅዕኖ አድርገዋል ለተባሉ የአገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች እውቅና ተሰጠ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአገር ውስጥ ደኅንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው ደም ሊያፋስሱ የሚችሉ ግጭቶችን በሽምግልና ላስታረቁ አባቶች ያላቸውን አድንቆት ገልጸው ተግባሩ ከአካባቢው አልፎ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለውታል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን ጋር በመተባበር

“ሁሉም ለሰላም፣ ሰላም ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ደሴ ከተማ ላይ ባዘጋጁት ኮንፈረንስ የአገር ሽማግሌዎቹና የኃይማኖት አባቶቹ ለበርካቶች ህይወት መጥፋት፣ ለንብረት ውድመትና ለአካባቢ አለመረጋጋት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ግጭቶችን በባህላዊ የሽምግልና ዘዴዎች ማክሸፋቸው ነው የተገለጸው፡፡

የአገሪቱን የፖለቲካ ትኩሳት ተከትሎ በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከግለሰቦች መበቃቀል ጀምሮ የመንግሥት መዋቅርን እስከ ማፍረስ፣ የህዝብ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እስከማድረስ፣ መንገዶችን ዘግቶ እንቅስቃሴን እስከማወክ የደረሱ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡

በባህላዊው የሽምግልና ጥረት ግን ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ እንደተቻለ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ እጅጉ መላኬ አስታወቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

"ሰላም ለሁሉም" የሰላም መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00


XS
SM
MD
LG