በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ ባለሥልጣናት በወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ሥር ዋሉ


ባህ ኢንዳው

የማሊ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ትናንት ሰኞ በወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ሥራ እንዳዋሏቸው ተገለጠ።

የቀደሙት ፕሬዚደንት ከጥቂት ወራት በፊት በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን በተወገዱባት ሃገር የጦር ሰራዊት መኮንኖቹ የወሰዱት ይህ እርምጃ የፖለቲካ ምስቅልቅሉን ሊያባብሰው እንደሚችል በርካታ ምንጮች መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ፕሬዚደንት ባህ ኢንዳው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞክታር ኩዋኔ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሱሊማኒ ዱኩሬ ከዋና ከተማዋ ከባማኮ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የጦር ሰፈር መወሰዳቸው ተገልጿል።

ዲፕሎማሲያዊ እና መንግሥታዊ ምንጮች እንደተናገሩት የጦር መኮንኖቹ እርምጃውን የወሰዱት የመንግሥት ባለስልጣናት የሽም ሽር ተካሂዶ ሁለት ወታደራዊ መኮንኖች ከነበራቸው የስልጣን ቦታ ከተነሱ በጥቂት ሰዐታት ውስጥ ነው።

ማሊ ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ የሀገሪቱ መሪዎች በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲልቀቁ ጠይቆ ያሰሩዋቸው ወገኖች በአድራጎታቸው ይጠየቃሉ ሲል አስጠንቅቋል።

XS
SM
MD
LG