በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት በሆንግ ኮንግ


ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ-19 ክትባት

የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ጊዜ ከማለፉ በፊት ክትባቱን የሚወስዱ በቂ ሰዎች ስለሌሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክትባቶችን በቅርቡ መጣል ሳይኖርብን አይቀርም ሲሉ የሆንግ ኮንግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሆንግ ኮንግ ከፋይዘር እና ከቻይና ሲኖቫክ ኩባኒያዎች ለሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮኑም ህዝቧ የሚበቃ ክትባት የገዛች ሲሆን የክትባት መርሃ ግብሩ ባለፈው የካቲት ወር ከተጀመረ ወዲህ የተከተቡት ሰዎች ብዛት 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የዓለም አካባቢዎች ክትባት ለማግኘት እየተሯሯጡ ባሉበት ሁኔታ እኛ ይህን ሁሉ ጥቅም ላይ ያልዋለ ክትባት ይዘን መቀመጣችን ያሉት የሆንግ ኮንጉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከአሁን ወዲያ ደግሞ ሌላ ክትባት አንገዛም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሆንግ ኮንግ ውስጥ ክትባቱን የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር እንዲያንስ ያደረገው በማኅበራዊ መገናኛ አማካይነት ስለክትባቱ የሚዛመተው ሃሰተኛ ወሬ፣ ከተማይቱ ውስጥ ቫይረሱ በብዛት ስላልተዛመተ ጉዳዩ አጣዳፊ ትኩረት ሳይሰጠው መቅረቱ እና ህዝቡ በሆንግ ኮንግ እና በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ያለው የጥርጣሬ አስተያየት እየተባባሰ መሆኑን ታዛቢዎች እንደምክንያት ያነሳሉ።

XS
SM
MD
LG