በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦቻ የትግራይ ወቅታዊ ሰብዓዊ ሁኔታ ሪፖርት


በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ኦቻ አሳሰበ።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5ነጥብ 2ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

XS
SM
MD
LG