በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 እና ክትባቱ


አርጀንቲናም በቫይረሱ የሚያዙት እና ለህልፈት የሚዳረጉት ሰዎች ቁጥር እጅግ እየጨመረ ነው

አርጀንቲናም በቫይረሱ የሚያዙት እና ለህልፈት የሚዳረጉት ሰዎች ቁጥር እጅግ እየጨመረ መምጣቱን በመግለጽ ከነገ ቅዳሜ የሚጀምር ጥብቅ የእንቅስቃሴ ክልከላ አውጃለች።

በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው የተላላፊ በሽታዎች አዋቂው እና የፕሬዚደንት ጆ ባይደን የህክምና ጉዳዮች ዋና አማካሪው ዶክተር አንተኒ ፋውቺ ዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንዳያሻቅብ መከላከል የምትችል ይመስለኛል ሲሉ ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ተናገሩ።

እንደ ፋውቺ ገለጻ ፕሬዚደንት ባይደን እስከ መጪው የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀን ጁላይ ፎር በሚኖረው ጊዜ ውስጥ ሰባ ከመቶው ህዝብ ቢያንስ አንድ ክትባት እንዲከተብ ያወጡት ግብ ተፈጻሚ ከሆነ እና አሁን በያዝነው የክትባት ፍጥነት ከቀጠልን የቫይረሱ ስርጭት እንደገና የሚያሻቅበት አደጋ ይገጥመናል ብዬ አልሰጋም ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እንዳያከትም ከተደቀኑት ከፍተኛ አደጋዎች አንዱ አስደንጋጭ የሆነው ደረጃ ያለው የተዛባ የክትባት ተደራሽነት ነው ሲሉ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ። ዶክተር ቴድሮስ ይህን ያሉት በዚሁ ሳምንት ውስጥ በጋራ ብልጽግና ኮመንዌልዝ አባል ሃገሮች የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር ነው።

"የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ እንዳሉት የክትባት አፓርታይድ ገጥሞናል " ሲሉ የጠቀሱት ዶክተር ቴድሮስ ባለከፍተኛ ገቢዎቹ ሃገሮች የህዝብ ብዛታቸው ከዓለም 15 ከመቶው ብቻ ሆኖ 45 ከመቶውን ክትባት ይዘዋል፥ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገሮች ደግሞ ከዐለም ህዝብ ግማሽ የሚሆነውን ይዘው የደረሳቸው የኮቪድ ክትባት 17 ከመቶ ብቻ ነው ሲሉ አነጻጽረዋል።

የተቀረው የዐለም አካባቢ የጤና ሰራተኞች ፥ ዕድሜአቸው የገፋ ሰዎችና ሌሎችም ለኮቪድ-19 በሽታ በይበልጥ ተጋላጭ የህብረተስብ ክፍሎች ክትባት ማዳረስ ሳይቻል ባለጸጎቹ ሃገሮች ልጆችንና ታዳጊዎችን መክተብ ጀምረዋል ያሉት የዐለም የጤና ድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ድርጅቱ ለዚህ መዛባት መፍትሄ ለማምጣት በርትቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG