በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ ተጠናቀቀ


650 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኃይማኖት አባቶችና ከሲቪክ ማኅበራት ጋር ግድቡን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም የኃይል መሥመር ዝርጋታው ግድቡ ከተገነባበት ጉባ አንስቶ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት እስከሚገኝበት ሆለታ ድረስ ተዘርግቷል ተብሏል፡፡

የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል ዶ/ር በለጠ ብርሃኑ፣ አሁን ላይ ከግንባታና ከኮንክሪት ሙሌት ጋር ተያይዞ የሚሰራው የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ሥራ 91.8 በመቶ መድረሱን ነው ጠቁመዋል፡፡

የግድቡ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ደግሞ 55.2በመቶ መድረሱንም ተናግረዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

በተጓዳኝም የግድቡ ሁለት ተርባይኖች የቅድመ ኃይል ምርት በመጪው ክረምት መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምርና ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር በለጠ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG