በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ በኮቪድ-19 ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር መዘገበች


ህንድ የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ቀን ከፍተኛው የሆነውን በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር መመዝገቧን አስታወቀች። ትናንት ማክሰኞ 4529 በኮቪድ-19 ሳቢያ መሞታቸውን ያረጋገጠች ሲሆን በአንድ ቀን ከ4500 በላይ ሲያልፍ የመጀመሪያ ጊዜው መሆኑ ታውቋል።

በህንድ ውስጥ እስካሁን ለቫይረሱ ከተጋለጡት ከ25 ነጥብ አራት ሰዎች ውስጥ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር 283 248 መድረሱንም ለማወቅ ተችሏል። በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ባጡ ሰዎች ቁጥር ከህንድ የሚበልጥ ቁጥር ያላት ዩናይትድ ስቴትስ ስትሆን አምስት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሽህ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል።

በህዝብ ብዛት ከዓለም ሁለተኛ በሆነችው በህንድ ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ መዛመቱ መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል። በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች እንዲሁም የሞቱት ሰዎች ቁጥር በይፋ ከሚታወቀው እንደሚበልጥ የጤና ጥበቃ አዋቂዎች ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG