በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ምዝገባ ላይ የተሰሙ ቅሬታዎች ከሀዋሳ


ሀዋሳ
ሀዋሳ

በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተፈፀመ ክፍተቶች ካሉ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ከቀናት በፊት የተጠናቀቀው የመራጮች ምዝገባ መዝገብ ከዛሬ ግንቦት 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ለታዛቢዎች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለህዝብ ክፍት ሆኗል።

በሃዋሳ ከተማ መዝገቦችን ተዘዋውረው የተመለከቱ የፖለቱካ ፓርቲዎች በመራጮች የምዝገባ ወቅት ኃላፊነት የጎደላቸው ያሏቸው ስህተቶች መፈፀማቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በዋናነት የጎላ ስህተት ፈፅመዋል ከተባሉ ጣቢያዎች ውስጥ ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡት የሃዋሳ ከተማ የምስራቅ ክፍለ ከተማ የውቅሮ ምርጫ ጣቢያ አንድ አስተባባሪ ስህተቱ መፈፀሙን አምነው እንደሚያርሟቸው ተናግሯል።

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ እና የደቡብ ክልል ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምርጫ ቦርድ መዝገቡን ክፍት ያደረገው እንደዚህ ዓይነት ስህተቶችን ለማረም ነው ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ምርጫ ምዝገባ ላይ የተሰሙ ቅሬታዎች ከሀዋሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00


XS
SM
MD
LG