በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማኅበረሰብ ደኅንነት ቅኝት የምክክር መድረክ - ባሕር ዳር


ፍሬዓለም ሽባባው

ኢትዮጵያ ውስጥ በከተሞች አካባቢ አሁን እየታየ ላለው የደህንነት ስጋት ምንጩ መዋቅሩ የተዛባ የፀጥታ ተቋማት በመኖሩ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው ገለፁ።

የዘጠኝ ክሎች እና የሁለት ክተማ አስተዳድሮች የፀጥታ አመራሮች የተሳተፉበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማኅበረሰብ ደኅንነት ቅኝት (ፓትሮል) የጋራ ምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በሰላም ሚኒስቴር እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በክልል ፀጥታ አመራሮች ትብብር በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው የለውጡ መንግሥት፣ ለማስወገድ ቃል ከገባቸው ችግሮች አንዱ ከፖለቲካ፣ ከዘር እና ከሀይማኖት ገለልተኛ የሆነ የፀጥታ ተቋም መገንባት ነው፤ በዚህ መሰረት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ ሰነድ ማዘጋጀት ተችሏል።

ወ/ሮ ፍሬዓለም በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ አሁን እየታየ ላለው የሰላም መደፍረስ ምንጩ የፀጥታ ተቋማት እንዝላልነት ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማኅበረሰብ ደኅንነት ቅኝት የምክክር መድረክ - ባሕር ዳር
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00


XS
SM
MD
LG