በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦነግ አመራር አባላት በነፃ እንዲለቀቁ ፍ/ቤት ወሰነ


የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና እና በአቶ ኪሲ ቂጡማ የሚጠሩ 13 ሰዎችን ልደታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በነፃ አሰናበታቸው።

ኮሎኔል ገመቹ አያና የሚገኙበት በአቶ ክስ ቅጡማ የሚጠራው መዝገብ ላይ የተከሰሱት ግለሰቦች የሽብር ጥቃት አድርሰዋል፣ አስተባብረዋል እና አሰማርተዋል ተብለው መከሰሳቸውን የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ገልፀዋል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረሽብር እና የህገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ ከሁለት ዓመት በኋላ ዛሬ ተከሳሾቹ በነፃ እንዲለቀቁ ብይን ሰጥቷል ሲሉ የተከሳሾቹ ጠበቃ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የኦነግ አመራር አባላት በነፃ እንዲለቀቁ ፍ/ቤት ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:51 0:00


XS
SM
MD
LG