በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት ያጠናቀቁ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ መዘዋወር ይችላሉ - የጤና ባለሥልጣናት


FILE - Pedestrians walk along Boston's fashionable Newbury Street in Massachusetts.

የኮቪድ-19 ክትባት ተከትበው ያጠናቀቁ ስዎች የአፍና አፍንጫ ጭንብል ሳያደርጉ መዘዋወር እንደሚችሉ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ግንኙነቶቻቸው አካላዊ ርቀት መጠበቅ ላያስለፍልጋቸው እንደሚችል የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሆኖም በህዝብ መጓጓዧዎች እና ሆስፒታሎች እንዲሁም ወህኒ ቤቶች እና ቤት የሌላቸው ሰዎች በሚጠለሉባቸው መኖሪያዎች በጭንብል መጠቀም አሁን ግዴታ መሆኑ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋሌንስኪ ንግድ ቤቶች እና ሌሎችም ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎች አሁንም ማስክ መጠቀም ግዴታ መሆኑ መቀጠል ይኖርበት እንደሆነ ያን ውሳኔ ለአካባቢው ባለሥልጣናት ትተውታል፤ ያለው የቫይረሱ ተጋላጭ ቁጥር እና የተከተቡ ሰዎች ብዛት ተመርኩዘው ሊወስኑት ይችላሉ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG