በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የባለድርሻ አካላት ሚና - በሀዋሳ


ሀዋሳ
ሀዋሳ

በስድስተኛው ሃገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ለሰላም እና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠት መንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ።

ምርጫው በበርካታ ስጋቶች እና ተስፋዎች የተሞላ መሆኑን በመገንዘብ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን መጭ ዕድል ላይ ለመወሰን የሚደረጉ የቀጠና እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጫናዎች ያሏቸውን መቋቋም የሚያስችል ሃገራዊ ትብብር እና ምክክር ያስፈልጋልም ብለዋል።

የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጅው የበየነመረብ ውይይት ከዩናይትድ ስቴትስ የተሳተፉ አንድ ከፍተኛ የሥነ አዕምሮ ሃኪምና ተመራማሪ በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ ላይ “ተከፍቷል” ያሉትን የስነ ልቦና እና የፕሮፖጋንዳ ጦርነት ለመመከት ሕዝቡ አንድነቱን ማጠናከር እና ብሄራዊ ጉዳዮችን ማስቀደም አለበት ሲሉ መክረዋል።

የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ “በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የባለድርሻ አካላት ሚና” በሚል ባካሄደው በበየነመረብ እና የፊት ለፊት ውይይት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ስድስተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ይሆን ዘንድ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ነው የገለጡት።

ይህንን ማድረግ የሚቻለውም ለሀገር ለመረጋጋት እና ለሰላም ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት መንቀሳቀስ ሲቻል ነው ያሉት።

በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አንዱ ነው። የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ ታምራት አሰፋ ሲናገሩ «የዘንድሮ ምርጫ በፈተናዎች የተሞላ ነው» ነበር ያሉት።

ከፈተናዎቹም ውስጥ “ከውጭ እየገጠመን ያለው” ያሉት ዓለም አቀፍ ጫና እና የምስራቅ አፍሪካ ጂኦፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ መሆኑን ጠቅሰው “ይህን ጫና የሚቀንስ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የባለድርሻ አካላት ሚና - በሀዋሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:05 0:00


XS
SM
MD
LG